አቶ መለስ የማስፈራራት መብት አላቸው? “ፍትሕ” ጋዜጣ በህትመት ዋጋ መወደድ ሳቢያ ‘ከምድረ ገጽ ይጠፋል’ ተብሎ ሲጠበቅ ዋጋውን ወደ 6 ብር ከፍ በማድረግ መንግሥትን የሚተችበትንም ቋንቋ በዚያው መጠን አሳድጎታል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት “የመለስ ሥልጣን ማስፈራራትንም ይጨምራልን?” በሚል ርእስ በርዕሰ አንቀጹ ባሰፈረው ጽሑፍ አቶ መለስ ያለገደብ በዜጎች ላይ የሚሰነዝሩትን ዛቻና ማስፈራርያዎች እንዲያቆሙ ጠይቋል፡፡ “ከ80 የማያንሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባሉበት አገር የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በሙሉ አሸባሪዎች ናቸው ማለት ከአገሪቱ ሕዝብ ግማሹ አሸባሪ ነው ብሎ እንደመወንጀል ነው፡፡” ካለ በኋላ “ፍትህ ጋዜጣ ጠ/ሚኒስትሩ በሕገ መንግሥቱ እና በሌሎች አዋጆች ከተሰጣቸው ሥልጣን ማለፋቸው አጥብቃ ትቃወማለች፤” ሲል አሳስቧል፡፡ —— “የሱዳኑ ባለሀብት የአንድ ቢልየን ብር የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን አ...
|
|||
No comments yet, be the first one to post comment.